ማስታወቂያ

programs top mid size ad

ፕ/ሮ መስፍን ወልደማሪያም

የእናንተን ጥያቄዎች ለፕ/ሮ መስፍን ወልደማሪያምእንዴት ሰነበታችሁ አድማጮቻችን? እንኳን ለአዲሱ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ!


ይህ የሸገር የቅዳሜ ጨዋታ አዘጋጅ መልዕክት ነው፡፡ 

ባለፉት ፮ ሳምንታት በቅዳሜ ጨዋታ የእንግዳ ዝግጅት አንጋፋው ምሁር ፕ/ሮ መስፍን ወልደማሪያም ሲያጨዋውቱን ሠንብተዋል፡፡

መዓዛ ብሩ ፕ/ሮ መስፍን ቢጠየቁ ብላ ያዘጋጀቻቸውን ጥያቄዎች ጠይቃ ፕሮፌሠሩም መልሠውላታል፡፡ በእናንተ በኩል ይህን ቢጠየቁ የምትሉት ወይንም የበለጠ ማብራሪያ የምትፈልጉበት ሀሳብ ካለ በ8101 አጭር የፅሁፍ መልዕክት መቀበያ prof አስቀድማችሁ ላኩልን ወይንም በኢሜል አድራሻ chawata@shegerfm.com ልትልኩልን ትችላላችሁ፡፡

መዓዛ ፕሮፌሠርን ቃል ባስገባቻቸው መሠረት ጥያቄዎቻችሁን ይዛ ለፕ/ሮ ታቀርባለች፡፡ 

አትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!

ሸገር FM 102.1 የናንተው ሬድዮ!

ቁልፍ ቃላት
Fri, 09/05/2014 - 19:10